የአገርዎ የፀረ ሙስና ሕጎች ምንድን ናቸው?
የፌዴራል የስነ-ምግባርና ጸረ-ሙስና ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ለማሻሻል የወጣ አዋጅ ቁጥር 1236/2021፣ የሀብት ማሳወቂያና ማስመዝገቢያ አዋጅ ቁጥር 668/2002፣ የተሻሻለው የፀረ ሙስና ልዩ ሥነ ሥርዓት እና የማስረጃ ህግ አዋጅ ቁጥር 434/1997፣ የወንጀል ሕግ አዋጅ ቁጥር 414/2004፤ የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ 1961፤ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸረ-የሙስና ኮንቬንሽንን ለማጸደቅ የወጣ አዋጅ ቁጥር 544/2007፣ የአፍሪካ ህብረት የሙስና መከላከያና መዋጊያ ኮንቬንሽን ለማጽደቅ የወጣ አዋጅ ቁጥር 545/1997፣ የኢጋድ የወንጀል ጉዳዮች የጋራ የፍትህ ትብብር ኮንቬንሽን ማጽደቂያ አዋጅ ቁጥር 732/2012፣ የኢጋድ አሳልፎ የመስጠት ኮንቬንሽን ማጽደቂያ አዋጅ ቁጥር 733/2004፣ የወንጀል ምስክሮችና ጠቋሚዎች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 699/2003; በወንጅል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረት ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣ አዋጅ ቁጥር 654/2002፣ የክልል የስነምግባር እና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጆች (ከ12 ክልሎች እና 2 ከተማ አስተዳደሮች ሕጎች አሏቸው)፣ የፌዴራል ዋና ኦዲተር ለማቋቋም የወጣ አዋጅ ማሻሻያ ቁጥር 1146/2011፣ የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006፣ ፈቃድ እና ቁጥጥር የባንክ ንግድ (የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ ቁጥር SBB/46/2010 የደንበኞች ተገቢ የባንክ ትጋት) እና የኢፌዲሪ አስፈጻሚ አካላት ስልጣንና ተግባር መወሰኛ አዋጅ 1263/2014.
ስልጣን የተሰጠዉ ፍርድ ቤት ከሚያስችልበት የቦታ ርቀት ጋር ተያይዞ የሚነሱ
ችግሮች፣
ለማጓጓዝ የሚወስደዉን ጊዜ ሳይጨምር ማንኛዉም ተጠርጣሪ በተያዘ በ48 ሰዐታት
ዉስጥ በአቅራቢያዉ ወደሚገኝ ፍርድ ቤት(በወንጀለኛ መቅጫ ስነስረዐት ህጉ አገላለፅ
በጣም አቅራቢያዉ ወደሆነዉ ፍርድ ቤት) ሊቀርብ እንደሚገባ በኢፌዴሪ ህገመንግስት
አንቀጽ 19/3 እና በወንጀለኛ መቅጫ ስነስረዐት ህግ ቁጥር 29 በግልጽ ተቀምጧል፡፡
የዚህ ድንጋጌ መሰረታዊ አላማ የተጠርጣሪን በአፋጣኝ በፍርድ ቤት የመጎብኘት መብት
22
(የተፋጠነ ፍትህ የማግኘት መብት) ማረጋገጥ መሆኑ ግልፅ ነዉ፡፡ ህብረተሰቡ
የተጠርጣሪን የተፋጠነ ፍትህ የማግኘት መብት እንዲጠበቅ የመፈለጉን ያህል
የተፈጸመዉ ወንጀል በምርመራ ተጋልጦ አጥፊዎች ለፍርድ እንዲቀርቡም ይፈልጋል፡፡
ይህን የህዝብ ፍላጎት ከማረጋገጥ አኳያ ፍርድ ቤቶች ሁለቱንም ፍላጎቶች በሚያማክል
(ባላንስ ባደረገ) መልኩ መስራት እንዳለባቸዉ አያከራክርም፡፡ ስለሆነም አንድ ተጠርጣሪ
ፍርድ ቤት እንደቀረበ ፍርድ ቤቱ በዋስ ሊለቀዉ አልያም ለመርማሪዉ የምርመራ
ቀነቀጠሮ በመፍቀድ በእስር እንዲቆይ ሊያዝ ይችላል(የወ/መ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር
59/2/3)፡ፍርድ ቤቱ ተጠርጣሪዉ በእስር ሆኖ ምርመራ እንዲጣራ ሲወስን ለዚህ ስራ
የሚሰጠዉ ቀነቀጠሮ በአንድ በኩል የተጠርጣሪን የተፋጠነ ፍትህ የማግኘት መብት
በሌላ በኩል ደግሞ መርማሪዉ የተፈጸመዉን የወንጀል ድርጊት በአግባቡ አጣርቶ
አጥፊዎችን ለፍርድ የማቅረብ ሀላፊነቱን እንዲወጣ የሚያስችል መሆን ይገባዋል፡፡
ይህን ለማረጋገጥ ደግሞ የዳኞች እዉቀት እጅግ ከፍተኛ ቦታ የሚሰጠዉ ነዉ፡፡
ከላይ እንደተቀመጠዉ የሙስና ወንጀል ክሶች እና ከምርመራ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ሁሉ
የሚታዩት በፌደራል ጠቅላይ ወይም ከፍተኛ ወይም በክልሉ ጠቅላይ እና ከፍተኛ
ፍርድ ቤት ነዉ፣በዚህ መሰረት ለህዝቡ ቅርብ የሆኑ የመጀመሪያ(ወረዳ) ፍርድ ቤቶች
ስልጣን የላቸዉም ማለት ነዉ፡፡ ስልጣኑ የተሰጣቸዉ ፍርድ ቤቶች ደግሞ በማዕከልና
በዞን ከተማ ደረጃ ላይ ያሉ በመሆናቸዉ ወንጀሉ ከተፈጸመበት ቦታ ወደነዚሁ ፍርድ
ቤቶች እየተመላለሱ ጊዜ ቀጠሮ መጠየቅ፣የብርበራ ወይም የመያዣ ወይም የንብረት
ዕግድ ትዕዛዝ ማግኘት በተግባር ሲታይ ከላይ በተጠቀሱተ የህዝብ ፍላጎት ላይ ትልቅ
እንቅፋት ይፈጥራል፡፡